®
speaker
Virtual
Great • Alfred • Nobel • Gives • Aspiration!
Nobel & Laureates' Ideas & Thought Processes!
Know Thyself Video

Alfred Nobel Video

501(C)3
Nonprofit Organization

Library Name Ganga

Translated to Amharic by Yordanos Mengistu

የቤተ-መጽሐፍት ስም ጋንጋ

አር.ቪ.ናጋቬኒ ኤም.ዲ.፣ ኤም.ኤስ. ፣ ጋንጋ ቤተ መጻሕፍትን መስራች

የጋንጋ ቤተ መፃህፍት የተሰየመው በውሃ አምላክ ጋንጋ ስም በተሰየመችው በአባቴ እናት ጋንጋማ ነው። አያቴ ጋንጋማ በጣም አስተዋይ፣ አፍቃሪ፣ አድልዎ የማታረግ እና በጎ አድራጊ ሴት ነበረች።

ይህ ገፅ የተሸነፉ ችግሮችን፣የተከፈለውን መስዋዕትነት፣ትጋትን፣የከፍተኛ ትምህርት ፍላጎትን፣የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን፣የተሸነፉ መሰናክሎችን እና አስቀያሚ አድሎአዊ ድርጊቶችን ለቁጥር በሚያታክቱ ተሸላሚዎችን ላይ ይገልፃል። እንዲሁም ለስደተኛ ተሸላሚዎች ተፈጻሚ የሚሆኑ የመርከብ መዝገቦችን ዋጋ ያሳያል። የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እድገት ሆነ ምንም ይሁን ምን ሰዎች ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን ለአንድ ነገር ወይም ሌላ ነገር ይጠይቃሉ።

የጋንጋማ አባት ተሟጋች ክሪሽናሙርቲ 2222 ማይል መንገድ ከካናታካ ግዛት ካዳባ መንደር ወደ ካሺ ከተማ በቅዱስ ወንዝ ጋንጋ በሶስት ወንዞች መጋጠሚያ አጠገብ ወዳለችው ካሺ ከተማ ተጓዘ። ሲመለስ ሁለተኛ ልጁ ተወለደ። ሕፃኑን ‘ጋንጋ’ ብሎ ጠራው።

Grandmother

አያት ጋንጋማ በ 331፣ 15 ኛ መስቀል፣ 2 ኛ ብሎክ፣ ጃያናጋራ፣ ቤንጋሉሩ 560011። ሞት: 10 ሚያዚያ 1976. ፎቶ: ታህሳስ 1968

Grandmother

በ አሜሪካ በሚኖረው በጎ አድራጊው አባቴ አር.ቪ.ራሚያ በተገዛ አኮርዲዮን አይነት ኮዳክ ካሜራ አያቴ ጋንጋማን ያነሳሁት ፎቶ

የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኞች ከሌሎች ይልቅ በልጆች እና በአረጋውያን ላይ የበለጠ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራሉ. እ.ኤ.አ. በ 1918 የተከሰተው የኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ ጤናማ ወጣት ጎልማሶችን ህይወት አጥፍቷል። በዚያ ወረርሽኝ የጋንጋማ ባል ቬንካኒያህ ታላቅ የሳምስክሪታ ምሁር እና የባለጸጋ የጋራ ቤተሰብ መሪ የሆነውበጎ አድራጊ አማችዋ ናራያናፓ በአስራ አምስት ቀናት ልዩነት አለፉ። ፍትህ የጎደላቸው የባሏ ወንድሞች ሴት በመሆኗ በአድሎ እና በስስት የራሷን መብት ከንብረቱ ነጥቀው መተዳደሪያ አሳጥተዋታል። ሀብታም እና በጎ አድራጎት የነበረችውን ሴት በድህነት እንድትማቅቅ አድርገዋል። ሁለቱ ልጆቿ አባቴ የሦስት ዓመቱ [ቬንካታ] ራሚያ እና ታናሽ እህቱ ነበሩ። በዚያን ጊዜ የጋንጋማ ደግ እና ተሟጋች የነበረው አባት ክርሽናሙርቲ ከዚህ አለም በሞት ተለየ። ከመቶ አመት በኋላ እንኳን በአብዛኛዎቹ ህንዳውያን ወንዶች ለሴቶች ያላቸውን አመለካከት በተመለከተ መ ሻሻል አልታየም።

በፎቶው ላይ ጋንጋማ በሞቃታማው የክረምት ፀሀይ ውስጥ የሚለውን የካናዳ ቻንዳማማን መጽሃፍ በማንበብ በጋራዡ ውስጥ እቤት የተነሳችው ነው።. ቤቱ የተገነባው መካኒካል ኢንጅነር በሆነው በጎ አድራጊ አባቴ አር.ቪ.ራሚያህ ሲሆን የተወለደው ራጊሙዳናሃሊ፣ ጉቢ ታሉክ ቱምኩሩ አውራጃ ውስጥ ነው። በኒው ዴሊ የአነስተኛ ደረጃ ኢንዱስትሪዎች ዳይሬክተር በነበረበት ጊዜ የሕንድ መንግሥት ማዕከላዊ የማሽን መሣሪያዎች ኢንስቲትዩት [አሁን ማዕከላዊ የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት] ወደሆነው ቱምኩሩ ጎዳና ቤንጋሉሩ ለማቋቋም ብቸኛ የጋራ ዳይሬክተር አድርጎ ወደ ቤንጋሉሩ አዛወረው። ተቋሙን ሲያቋቁም የህንድ መንግስት የኢንስቲትዩቱን ዳይሬክተርነት ቦታን ከልክሎታል። እሱም ወደ ቀድሞ የዳይሬክተርነት ቦታው መመለስን መርጧል ከዛም ወደ ቤንጋሉሩ ቢሮ ተዘዋውሯል። ራጃጂናጋራ የአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት ተቋም ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ በ 54 ዓመቱ በወጣትነት በቤንጋሉር አረፉ።

Ramiah

መካኒካል ኢንጅነር አር.ቪ.ራሚያህ በጠየቀው መሰረት የወርቅ ሜዳሊያውን በመተካት ቦርሳውን ከ50 ሩፒ ጋር ይዞ። ሞት የካቲት 13 ቀን 1969

ሁልጊዜ ራምያ ትምህርት በሚማርበት ጊዜ የመጀመሪያውን ደረጃ ነበር የሚያገኘው። የፊዚክስ ኩክ ሽልማትም አሸንፏል። አንደኛ ደረጃ ማግኘቱን ለማረጋገጥ ብቻ የፈተናውን ውጤት በማጣራት ካስመዘገበው በላይ ማንም እንዳስመዘገበ እና ሁለተኛ ደረጃ እንዳልወጣ ያረጋግጣል። በኢንጂነሪንግ የመጀመሪያ ደረጃን ሲያገኝ ሸላሚውን ንጉስ ማሃራጃ ክሪሽናራጃ ኦዴያርን በወርቅ ሜዳሊያ ምትክ በጥሬ ገንዘብ ጠየቀ።

Bahadur

ልዑል ማሃራጃ ናልዋዲ ክሪሽናራጃ ኦዴያር ባሃዱር IV እና ሙሽራዋ ራና ፕራታፕ ኩማሪ የካቲያዋር ፣ 1900። ሰዓሊ፡ ራጃ ራቪ ቫርማ። ፎቶግራፍ አንሺ: ሩፒካ ሻውላ ምንጭ፡ ዊኪፔዲያ

ወደ አሜሪካ ከመሄዴ በፊት የእናቴ እናት አያቴ ሳንናማ አንድ ታሪክ ነገረቺኝ። ራሚያህ በስሪ ጃያቻማራጄንድራ የሙያ ተቋም [አሁን ፖሊቴክኒክ] ቤንጋሉሩ ፋኩልቲ አባል ነበር። የህንድ መንግስት በአሜሪካ ውስጥ ለድህረ ምረቃ ትምህርት የነፃ ትምህርት ዕድል እየሰጠ ነበር። የሚያስፈልገው ዲግሪ ነበር። ፕሮቶኮሉን በማክበር 'በተገቢው መንገድ' ተብሎ በሚታመነው ወደ ህንድ መንግስት እንዲያስተላልፍለት ማመልከቻውን ለአሰሪው አስገባ። ጭፍን ጥላቻ ያደረባቸው አለቆቹ ብራህማና * [አንግሊዝድ ብራህሚን*] ስለነበር ብቻ ማመልከቻውን አላስተላለፉትም። ለህንድ መንግስት በተቋማቸው ውስጥ የዲግሪ ተቀጣሪ የለም ብለው በመዋሸት ከዲግሪ በታች ዲፕሎማ የያዙ ሰራተኞችን ማመልከቻ አስተላለፉ።

*አብዛኞቹ የሳናታና ድሀርማ [ሂንዱ] የኖቤል ተሸላሚዎች ብራህማናስ [ብራህሚንስ] ናቸው። ከባሃራታ [ህንድ] በተለየ መልኩ በሳይንስ የላቁ አገሮች እና የኖቤል ተሸላሚ ኮሚቴዎች ብራህማንስ [ብራህሚንስ] ላይ አድልዎ አያደርጉም። በብዙ ማህበረሰቦች ላይ ተመሳሳይ መድልዎ በአለም ዙሪያ አለ።

Wavell

የህንድ ምክትል ማርሻል አቶ አርኪባልድ ፐርሲቫል ዋቭል በዴሊ በሚገኘው ዴስኩ ላይ።

ራሚያ ይህን ውሸት እና መድልዎ ሲያውቅ ስኮላርሺፕን ለማጽደቅ ባለስልጣን ለነበረው በብሪታንያ ስር ለነበረው የህንድ ከፍተኛ መኮንን ቪሲሮይ ዋቭል ዲግሪ እንዳለው ጻፈ። ቪሲሮይ ዋቭልም ለቃለ መጠይቅ ወደ ዴልሂ ጋበዘው። ጠያቂዎቹ ስለኬሚስትሪ ጠየቁት። መሐንዲስ ለመሆን ለሚፈልጉ ተማሪዎች ኬሚስትሪ አስፈላጊ አልነበረም ሲል ምላሹን ሰጥቷል። ጊዜ ቢሰጠው ለጥያቄያቸው መልስ እንደሚሰጥም አክሏል። በሚቀጥለው ቀን ከቀትር በኋላ በ4 ሰዓት እንዲመለስ ነገሩት። በማግስቱም የኬሚስትሪ ጥያቄያቸውን መለሰላቸው።ከዛም ስኮላርሺፑን ተሸልሟል። ራሚያ ሴቶችን ጨምሮ ሁሉንም ሰው እንዲማሩ ይፈልግ ነበር።

Records

የዩኤስ ባህር ሃይል፣ ኒውዮርክ፣ ታህሳስ 28 ቀን 1945፣ የመርከብ መድረሻ መዝገብ፣ የዩኤስ መዛግብት፣ ዋሽንግተን ዲሲ

passenger list

የአሜሪካ የባህር ኃይል፣ ኒው ዮርክ፣ ታህሳስ 28 ቀን 1945፣ የተሳፋሪዎች ዝርዝር፣ የዩኤስ መዛግብት፣ ዋሽንግተን ዲሲ።

ህንዳዊው ሲቪል ራምያህ እ.ኤ.አ. ህዳር 30 ቀን በ1945 ከካልካታ [ኮልካታ] በአሜሪካ የባህር ኃይል መርከብ ወደ አሜሪካ በመጓዝ በአዮዋ ስቴት ኮሌጅ [አሁን በአዮዋ ስቴት ዩኒቨርሲቲ] የግብርና ማሽኖች የሁለት አመት የምረቃ ፕሮግራ ለመማር ሄደ። ፕሮግራሙን በአንድ ዓመት ተኩል ውስጥ አጠናቀቀ።ከዛ ሲመለስ ባመጣው የአኮርዲዮን አይነት ኮዳክ ካሜራ አያቴ ጋንጋማን ፎቶግራፍ አንስቻለሁ።

በአሜሪካ፣ ፔንስልቬንያ ጎዳና፣ ዋሽንግተን ዲሲ፣ የሚገኘው የታሪክ ምሁሩ ፖል ህንድ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ባትሳተፍም በጎረቤት በርማ [ሚያንማር] ውስጥ የአሜሪካ ወታደሮች እንደነበሩ ገልፆልኛል። ጦርነቱ ሲያበቃ ወታደሮቹ ለመርዳት በእነዚህ አገሮች ውስጥ ቆዩ. ወደ አሜሪካ ለመመለስ እና በመርከብ ለመሳፈር ወደብ ያስፈልጋቸው ነበር። ካልካታ ከበርማ ድንበር ጋር ቅርብ ነው። አሜሪካ ስደተኞችን የምትቀበለው ከአውሮፓ ብቻ ነው። ይህ ሊቨርፑል፣ እንግሊዝ ቢሆን ኖሮ ወደ አሜሪካ የሚመጣ የመንገደኞች መርከብ ይኖር ነበር። ከዛ በኋላ ነበር አሜሪካ የስደተኞች ህግን ቀይራ በችሎታ ላይ ተመስርታ ስደተኞችን መቀበል የጀመረችው። በተሳፋሪው ዝርዝር ውስጥ ያሉት ጥቂት ህንዳውያን ሁሉም ወጣት ወንዶች ናቸው ምናልባትም ብዙዎቹ ለድህረ ምረቃ ትምህርት ወደ አሜሪካ የመጡ ናቸው።

Grandparents

የእናቴ እናት እና አባት ቲ.ራማ ራኦ እና ሳናማ ብዙ ጊዜ "አንድ ሰው ምጽዋት ማድረግ አለበት" ትላለች።

የእናቴ ውንድ ቅድመ አያት አሽዋቲያ ልጅ ለማግኘት 4444 ማይል በእግሩ ተጉዘው ከቲሩማከዳሉ ካርናታካ መንደር ሁለት ጊዜ ወደ ካሺ ጉዞ አድርገዋል። ከዚያም አንድ ልጃቸው ናንጁንዲህ፣ ታህሲልዳር ተወለደ። የናንጁንዲህ ልጅ እና አማች ቅድመ አያቶቼ ቲ.ራማ ራኦ እና ሳናማ ከምክንያታዊነት በላይ ሄደዋል። ሲቪል መሐንዲስ ቲ.ራማ ራኦ ለመግለጽ በሚያስቸግር መልኩ የዋህ እና ታጋሽ ነበሩ። ፈታኙን የሁሊኬር መሿለኪያን ከገነባ በኋላ መሿለኪያ ራማ ራኦ በመባልም ይታወቅ ነበር። ከአቶ ኤም ቪሽቬሽቫራያ ጋር፣ የክርሽና ራጃ ሳጋራ ግድብን እና አጎራባች የብሪንዳቫን የአትክልት ስፍራን ገነባ። የብሔራዊ ምህንድስና ተቋም ሚሱሩ መስራችም ነበር። ጎበዙ ሳንናማ የ ቤት እመቤት በመሆን ትልቅ ቤተሰብን አስተዳድራለች እናም ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ዘመዶቻቸውን እና ሌሎችን በቤታቸው በመደገፍ እና ለማሃራጃ ሳምስክሪታ ኮሌጅ ተማሪዎች ነፃ ምግብ አቅርባለች። የሰዎችን አእምሮም ከውስጥ እና ከውጪ ታውቃለች። ሁሌም "አንድ ሰው ምጽዋት ማድረግ አለበት" ትላለች የጋንጋ ቤተ መፃህፍትን ለማቋቋም ብዙ ጊዜ እነዚህን ቃላት መስማት ትልቅ አስተዋፅዖ አድርጎልኛል።

የኖቤልሊስቶችን የህይወት ታሪክ አነባለሁ። ይህ የማንበብ ልምድ ወደ ባለራዕይ ሥራ ፈጣሪነት እንዲሁም መላው ዓለም ወደሚጠቅም ጋንጋ ቤተ መጻሕፍነት አድጓል።

India map

ወንዝ ጋንጋ ፎቶ: ዊኪፔዲያ

ኃያሉ የጋንጋ ወንዝ አስራ አንድ ገባር ወንዞችን ያሉት ሲሆም እነሱ ደሞ የራሳቸውን ገባር ወንዞች ያላቸው፣ የሚሰፋ፣ የሚፈሱ እና ብዙ ሰዎችን የሚጠቅሙ በመጨረሻም ወደ ውቅያኖስ በመፍሰስ መላውን አለም ይጠቅማሉ። ሳይንሳዊ ግኝቶች እና የሰላም እንቅስቃሴ ልክ እንደ ጋንጋ ወንዝ በትንሹ የሚጀምሩ እና ተመሳሳይ ንድፍ የሚከተሉ ናቸው።

Discover Your Abilities and Aspirations!

$10 $25 $50 $100 Other
Tax Exempt 501(c)3 Non-Profit Organization
Any Currency

“One comes to be of just such stuff as that on which the mind is set” - Maithri Upanishath, VI.34:3

“…the peace that is found in libraries and laboratories…” - Louis Pasteur
Contact Us E-Mail: Ganga@GangaLibrary.org
Ganga library non-profit 501(c)(3) org. Contributions tax deductible. IRS Tax ID 46-2892728

Copyright © 2022 Ganga Library Inc.   All Rights reserved.;